+251 900 14 14 14/ +251 900 15 15 15

ስለ እኛ/About Us

“ኢትዮጵያን እናክማት!” ፡- በኢፌዲሪ ሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከጥቅምት 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘ እና በቦርድ የሚመራ ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡

“ኢትዮጵያን እናክማት!” ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት፡- ይህን ‹‹የዓለም አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ቀን በኢትዮጵያ›› የተሰኘውን በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለውን መርሀ-ግብር ከተለያዩ መንግስታዊ፣ ሀገር በቀልና ዓለማቀፋዊ ተቋማት ጋር በመተባበር ሲያሰናዳ፤ የሁሉም ሀገራት አምባሳደሮችን ዲፕሎማቶች፤ ሀገርን አህጉርንና ዓለምን በተለያዩ አውዶች የሚያገናኙና የሚያቀራርቡ መሆናቸውን በማጤን ነው፡፡

ለዚህም ‹‹ኢትዮጵያ ለ ዓለም ፤ ዓለም ለ ኢትዮጵያ›› በሚል ኃይለ ቃል የሚከናወኑ የተለያዩ መርሀ-ግብሮችን በመላው ዓለም ለሚኖሩ የዓለማችን ሀገራት ዜጎች ተደራሽ በሚሆን መልኩ አሰናድቶ ተፈጻሚ ለማድረግ፤ በመላው ዓለም የምትኖሩ የሀገራት ተወካይ የሆናችሁ፤ ውድ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ ተቋማቶች፤ ባሕላችሁን፣ ትውፊታችሁን፣ ኃይማኖታችሁን፣ቴክኖሎጂያችሁን፣ ጥበባችሁን፣ ሰብአዊነታችሁን፣ በጎ አድራጎታችሁን እና ልማታችሁን በማንገብ ከተለያ ሀገራት መሰል ክንውኖች ጋር፤ትውውቅና ልምድ ልውውጥ ማከናወን ትችሉ ዘንድ በኢትዮጵያነት ክብርና ፍቅር የተሳትፎ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
Read More...

የቦርድ አባላት/Board Members

‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት በተቋም ደረጃም፡- የራሱን ዲጂታል ስቱዲዮ፣የአይቲ ስታፍ፣የዝግጅትና ፕሮሞሽን ስታፍ፣መጠነኛ የቁሳቁሶች ማከማቻ፣ የዝግጅቶች መድረክ እንዲሁም አጠቃላይ የማኔጅመንት ቢሮ የተዘጋጀለት ሲሆን ፤ በዲጂታል ስቱዲዮ፡- ራሱን የቻለ የሚዲያ ፕላት ፎርም፣ የተለያዩ የቅስቀሳ ሙዚቃዎች፣ዘጋቢ ፊልሞች፣የተለያዩ ዘውግ ያላቸው ማስታወቂያዎች እንዲሁም ይህን/እየተጠቀምንበት የምንገኘውን የሎተሪውን በይነ መረብ/ዌብሳይትን ጨምሮ የተለያዩ በርካታ ቅድመ ሥራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

ይተኮር፡- ‹‹ የዓለም አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ቀን በኢትዮጵያ!›› ፕሮጀክት አመራሮች በ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ሲሆን፤ በዘር፣በጎሳ፣በኃይማኖት፣በፖለቲካ፣በወገንተኝነት፣ ባጠቃላይ በራስወዳድነትና በክፋት ሠንሰለት ያልተተበተቡ ሲሆን ሰውነትን በማስቀደም ለወገንና ለሀገር ፈጥኖ ደራሽ ሆነው ‹‹ኢትዮጵያን ለ ዓለም፤ዓለም ለ ኢትዮጵያውያ›› በሚል ኃይለ ቃል በታማኝነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ደበበ እሸቱ

የጥበብ ሰው

ደራርቱ ቱሉ

አትሌት

ኡዝታስ አቡበከር አህመድ

የኢስላሚክ ጥናቶች ምሁር